ሐሰት: ይህ ቪዲዮ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ሲደበደቡ አያሳይም

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ሲደበደቡ ያሳያል በሚል ኢንስታግራም ላይ የተጋራው ይህ ልጥፍ ሐሰተኛ ነው።
ቪዲዮው ላይ ያለው ጽሁፍ “የኢስራኤል ጠቅላይ ሚር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ተደበደቡ” ይላል።

ጉግልን በመጠቀም የተደረገው የምስል ፍለጋ ውጤት ቪዲዮው ኔታንያሁ ሲደበደቡ አያሳይም።
ዘ ታይምስ ኦፍ ኢዝራኤል ቪዲዮውን መስከረም 10 ቀን 2018 ዓ.ም በድረ-ገጹ ላይ አጋርቶት ነበር። ሪፖርቱ የ70 ዓመቱ የሕግ አውጪ እና የክኔሴት (የፓርላማ) አባል የሆኑት ኤሊ ዳላል በመስከረም ወር 2018 ዓ.ም ገዢው ፓርቲ በከፋር ሳባ በተካሄደው ሰልፍ ላይ በሚያልፉበት ወቅት መውደቃቸውን ያብራራል።
በእስራኤል ውስጥ የቀኝ ክንፍ የፖለቲካ ፓርቲ የሆነው ሊኩድ የሚመራው በኔታንያሁ ነው።
እዚህ እና እዚህ ጋር እንደሚታየው ቪዲዮው በኤክስ (ቀደም ሲል ትዊተር በሚታወቀው ) አካውንቶች ላይ ዳላል በተቃውሞ ሰልፈኞች መካከል ለማለፍ ሲሞክሩ እንደወደቁ ከሚገልጽ ማብራሪያ ጋር ተጋርቷል።
በተጨማሪም ዘ ጀሩሳሌም ፖስት ዳላል በኩፋር ሳባ ላይ በተካሄደው ተቃውሞ ወቅት ተገፍተው መደቃቸውን ዘግቧል።
ፔሳቼክ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ሲደበደቡ ያሳያል በሚል ኢንስታግራም ላይ የተጋራውን ልጥፍ መርምሮ ሐሰተኛ መሆኑን አረጋግጧል።
ይህ ልጥፍ በፌስቡክ እና በተለያዩ የማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የፔሳ ቼክ የእውነታ መርማሪዎች በተከታታይ የሚያደርጉት የመረጃ ማረጋገጥ እና የተሳሳተ መረጃን የማጋለጥ ተግባር አካል ነው።
እንደ ፔሳቼክ ያሉ ገለልተኛ ሶስተኛ ወገን የእውነት መርማሪ ድርጅቶች ከፌስቡክ እና መሰል የማህበራዊ ድረ ገጾች ጋር በመጣመር የሐሰት ዜናን መለየት እንዲያስችልዎ ይሰራሉ:: ይህን የምናደርገውም በየማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የሚመለከቱት ልጥፍ/ መረጃ መነሻቸውን በማያያዝ እና ጠለቅ ያለ ዕይታ እንዲኖርዎ በማድረግ ነው::
በፌስ ቡክ ላይ የሐሰተኛ መረጃ ወይም የተጭበረበረ የመሰልዎ አጋጣሚ አለ? እንግድያውስ በእዚህ መንገድ ጥቆማ መስጠት ይችላሉ:: እንዲሁም ይህን ተጨማሪ ኢንፎርሜሽን በመጠቀም አጠራጣሪ መልዕክቶችን ለመለየት የፔሳቼክ መንገዶችን ማየት ይችላሉ::

ይህ የእውነታ ምርመራ የተዘጋጀው መቀመጫቸውን ኢትዮጵያ ባደረጉ የፔሳቼክ እውነታ አጣሪዎች (ስማቸው ለደህንነታቸው ሲባል ያልተገለጸ) ሲሆን በፔሳቼክ ሲንየር ኮፒ ኤዲተር ሜሪ ሚቲሰያ አርትኦት፤ የቀረበ ነው።
ጽሑፉ በፔሳቼክ ማኔጂንግ ኤዲተር ስቴፈን ንድግዋ እንዲታተም ጸድቋል።

ፔሳቼክ የምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የፋይናንስ መረጃ መርማሪ ተቋም ነው:: ካትሪን ጊቼሩ እና ጀስቲን አርንስቴን በተባሉ ሰዎች የተመሰረተ እንዲሁም በአህጉሪቱ ትልቁ የሲቪክ ቴክኖሎጂ እና የጋዜጠኝነት መረጃ ቋት አቅራቢ በኮድ አፍሪካ የተገነባ ነው:: እንደ ጤና : የገጠር ልማት እና የንጹህ ውሃ አቅርቦት በመሳሰሉ መስኮች ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ከመንግስት የሚጠበቁ አቅርቦቶች ላይ የተጨባጩን ዓለም እይታችንን ሊቀርጹ የሚችሉ በይፋ በሚሰራጩ የፋይናንንስ መረጃዎችን ዙርያ ህብረተሰቡ እውነተኛ መረጃን ማገናዘብ እንዲችል ለማገዝ የሚያስችል ድጋፍ ይሰጣል:: ፔሳቼክ ሚድያዎች የሚያቀርቡትን ጥንቅርም ይፈትናል:: የበለጠ መረጃ ለማግኘት pesacheck.org. ይጎብኙ::
ፔሳቼክ ኮድ ፎር አፍሪካ ከዶቼቬለ አካዳሚያ ባገኘው ድጋፍ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሚድያዎች እንዲሁም የሲቪክ ተቋማት ጋር በመተባበር ኢኖቬት አፍሪካ ፈንድ በሚለው መስመሩ የሚያቀርበው እንቅስቃሴ ነው::



