ሐሰት: የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ከምርጫው ቀን በፊት በኢትዮጵያ ጅማ አልተሰራጩም

ከምርጫው ቀን በፊት በኢትዮጵያ ጅማ ውስጥ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሰራጩትን የድምጽ መስጫ ወረቀቶችን ያሳያል የሚለው የትዊተር ልጥፍ ሐሰተኛ ነው።
የትዊተር ልጥፍ ጽሁፉ “ይህ መራጮች ድምጻቸውን ለመስጠት ሲመጡ የምርጫው ቀን መሰጠት የነበረበት የመራጮች የድምጽ መስጫ ወረቀት ነው። ነገር ግን ይህ የመራጮች የድምጽ መስጫ ወረቀት ከምርጫው ቀን በፊት በጅማ በየመንገዱ ለህዝቡ ታድሏል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምላሽ ሊሰጥበት ይገባል” ይላል።

ልጥፉ የብልጽግና ፓርቲ እጩዎችን ስም እና የፓርቲውን የምርጫ ምልክት በያዙ ሶስት የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ታጅቧል።
የቅድመ ምርጫው ሂደት ተጭበርብሯል የሚሉ በርካታ ዘገባዎች ኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልልን ከመሳሰሉ ክልሎች ሲወጡ ነበር።
የዎላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ እና የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ሰኔ 05 ቀን 2013 ዓ.ም በጋራ በመሆን በሰጡት መግለጫ የገዢው ፓርቲ አባላት ለአንድ ግለሰብ እስከ 90 የሚደርስ የመራጮች ካርድ እንደሰጡ፣ ባልታወቁ ሰዎች ስም የመራጮች መታወቂያ ካርዶችን እንደወሰዱ፣ ለደጋፊዎቻቸው የመራጮች መታወቂያ ካርድ እየሰጡ ለተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች ደግሞ እየከለከሉ መሆኑን እና የሁለቱ ፓርቲ አባላት ላይ ማዋከብ እና እስር እየተፈጸመ እንደሆነ ገልጸዋል።
ሚያዚያ 28 ቀን 2013 ዓ.ም ደግሞ የኦሮሞን ህዝብ እና የኦሮሚያን ክልል የሚመለከቱ ጉዳዮችንበመዘገብ የሚታወቀው ኦኤምኤን የተባለው የቴሌቭዥን ጣቢያ ግለሰቦች ከሱቆች ሸቀጦችን ለመግዛት የምርጫ ካርዳቸውን እንዲያሳዩ እየተጠየቁ እንደሆነ እና የመራጮች ካርድ በክልሉ በህገ-ወጥ መንገድ እየተሰራጨ መሆኑን ዘግቧል።
እንዲሁም አራት የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የግል እጩዎች በሶማሌ ክልል ውስጥ ከምርጫ ማጭበርበር ጋር የተያያዙት ችግሮች እስከሚፈቱ ድረስ በክልሉ እንደማይወዳደሩ በጋራ ባወጡት መግለጫ አሳውቀዋል።
በተጨማሪም ሰባት ሀገር አቀፍ እና ክልላዊ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሰኔ 06 ቀን 2013 ዓ.ም በጋራ በሰጡት መግለጫ በምርጫው ሂደቱ ላይ ያላቸውን ቅሬታ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተወሰኑትን ችግሮች አምኖ በመቀበል እና ከምርጫ ቦርድ እውቅና ውጪ ተከፍተው መራጮችን ሲመዘግቡ የነበሩ 79 የምርጫ ጣቢያዎች በአዲስ አበባ፣ በድሬደዋ እና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች እንደነበሩ በመታወቁ እዛ አካባቢ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የተደረገውን የመራጮች ምዝገባ መሰረዙን አሳውቋል።
በተመሳሳይ መልኩ በሐረሪ እና በሶማሌ ክልሎች ድምጽ የመስጠቱ ሂደት ከቅድመ ምርጫው ሂደት ጋር በተያይዙ ችግሮች፣ በጸጥታ መደፍረስ እና በድምጽ መስጫ ወረቀቶች ህትመት ችግር ምክንያት ወደ ጷጉሜ 01 ቀን 2013 ዓ.ም ተላልፏል። ከሐረሪ እና ሶማሌ ክልሎች በተጨማሪ ጷጉሜ 01 ቀን 2013 ዓ.ም በሁለተኛው ዙርያ ምርጫ የሚካሄድባቸው በሌሎች ክልሎች የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎችም አሉ ።
ምንም እንኳን በአንዳንድ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ከምርጫው መጭበርበር ጋር የተያያዙ ዘገባዎች ቢቀርቡም ከምርጫው ቀን በፊት በኢትዮጵያ ጅማ ውስጥ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ለህብረተሰቡ ተሰራጭተዋል የሚለው ክስ እውነት አይደለም።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተግባቦት አማካሪ የተባለውን ነገር ሐሰት ነው በማለት ውድቅ ካደረጉ በኃላ የእውነተኛውን የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ምስሎች ይፋ አድርገዋል።

ፔሳቼክ ከምርጫው ቀን በፊት በኢትዮጵያ ጅማ ውስጥ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሰራጩትን የድምጽ መስጫ ወረቀቶችን ያሳያል የሚለውን የትዊተር ጽሁፍ ተመልክቶ ሐሰት መሆኑን አረጋግጧል።
ይህ ልጥፍ በፌስቡክ እና በተለያዩ የማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የፔሳ ቼክ የእውነታ መርማሪዎች በተከታታይ የሚያደርጉት የመረጃ ማረጋገጥ እና የተሳሳተ መረጃን የማጋለጥ ተግባር አካል ነው::
እንደ ፔሳቼክ ያሉ ገለልተኛ ሶስተኛ ወገን የእውነት መርማሪ ድርጅቶች ከፌስቡክ እና የማህበራዊ ድረ ገጾች ጋር በመጣመር የሐሰት ዜናን መለየት እንዲያስችልዎ ይሰራሉ:: ይህን የምናደርገውም በየማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የሚመለከቱት ልጥፍ/ መረጃ መነሻቸውን በማያያዝ እና ጠለቅ ያለ ዕይታ እንዲኖርዎ በማድረግ ነው::
በፌስ ቡክ ላይ የሐሰተኛ መረጃ ወይም የተጭበረበረ የመሰልዎ አጋጣሚ አለ?እንግድያውስ በእዚህ መንገድ ጥቆማ መስጠት ይችላሉ::እንዲሁም ይህን ተጨማሪ ኢንፎርሜሽን በመጠቀም አጠራጣሪ መልዕክቶችን ለመለየት የፔሳቼክ መንገዶችን ማየት ይችላሉ::

ይህ የእውነታ ምርመራ በፔሳቼክ የእውነታ አጣሪ በኪያ አሊ ተጽፎ በፔሳቼክ ኮፒ ኤዲተር ኤደን ብርሃኔና በፔሳቼክ ም/አዘጋጅ ሮዝ ሉካሎ አርትኦት፤ የቀረበ ነው::
አንቀጹ ለህትመት እንዲበቃ ያረጋገጠው ደግሞ የፔሳቼክ ዋ/አዘጋጅ ኤኖክ ናያርኪ ነው::

ፔሳቼክ የምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የፋይናንስ መረጃ መርማሪ ተቋም ነው:: ካትሪን ጊቼሩ እና ጀስቲን አርንስቴን በተባሉ ሰዎች የተመሰረተ እንዲሁም በአህጉሪቱ ትልቁ የሲቪክ ቴክኖሎጂ እና የጋዜጠኝነት መረጃ ቋት አቅራቢ በኮድ አፍሪካ የተገነባ ነው:: እንደ ጤና : የገጠር ልማት እና የንጹህ ውሃ አቅርቦት በመሳሰሉ መስኮች ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ከመንግስት የሚጠበቁ አቅርቦቶች ላይ የተጨባጩን ዓለም እይታችንን ሊቀርጹ የሚችሉ በይፋ በሚሰራጩ የፋይናንንስ መረጃዎችን ዙርያ ህብረተሰቡ እውነተኛ መረጃን ማገናዘብ እንዲችል ለማገዝ የሚያስችል ድጋፍ ይሰጣል:: ፔሳቼክ ሚድያዎች የሚያቀርቡትን ጥንቅርም ይፈትናል:: የበለጠ መረጃ ለማግኘት pesacheck.org. ይጎብኙ::
ፔሳቼክ ኮድ ፎር አፍሪካ ከዶቼቬለ አካዳሚያ ባገኘው ድጋፍ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሚድያዎች እንዲሁም የሲቪክ ተቋማት ጋር በመተባበር ኢኖቬት አፍሪካ ፈንድ በሚለው መስመሩ የሚያቀርበው እንቅስቃሴ ነው::


