ሐሰት: የኤርትራ እና የኢትዮጵያን ባንዲራን ወታደሮች ሲያውለበልቡ የሚያሳየው ፎቶ የፈጠራ ነው።

የትግራይ ክልል፣ የኤርትራ እና የኢትዮጵያን ባንዲራዎች ወታደሮች ሲያውለበልቡ ያሳያል በሚል ፌስቡክ ላይ የተለጠፈው ይህ ምስል ሐሰተኛ ነው።
ፎቶውን ያጀበው ጽሁፍ “ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከሰይጣንም ጋር ቢሆን እንደምታብሩ የታወቀ ነው ዳሩ ግን ከሳምንት የማያልፍ ግርግር በመፍጠር የግለሰቦች ሀብት ማካበቻ ከመሆን ያለፈ 10 ሁናችሁም ብትደራጁ የምታመጡት አንዳች ነገር የለም!!! ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር” ይላል።
ይኸው ምስል እዚህ ገጽ ላይም “ይህ ይግባችሁ። ሰሜናውያን ኦሮሚያን እንጂ ኦሮሞዎችን አይወዱም። አንዳንዶቻችን መቼ ይሆን ይህንን የምንገነዘበው? የቅኝ ገዢዎችን ስምምነት ከሕዝባችን ክብር ይልቅ የሚመርጡ ሰዎች እውነተኛ ዓላማቸው ግልጽ ነው። ይህም የግል ጥቅም እንጂ ብሔራዊ ነፃነት አይደለም። ግልጽ ነው። በጭቆና ላይ የተገነቡ ጥምረቶችን መቃወም አለብን። ከቅኝ ገዢ ኃይሎች ጋር መተባበር የሞራል ህጋዊነት አያስገኝም። ቅኝ ገዢዎች ነፃ አውጪዎች ሊሆኑ አይችሉም። ከታሪክ ተማሩ።” በሚል ከተተረጎመ የእንግሊዘኛው ጽሁፍ ጋር ተጋርቷል።

ጉግልን በመጠቀም የተደረገው የምስል ፍለጋ ውጤት ያስገኘው የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን ብቻ ነው።
ፔሳቼክ በመጣራት ላይ ያለው ምስል ውስጥ በርካታ ጉድለቶችን ተመልክቷል። ለምሳሌ የትግራይ ክልል ባንዲራ በቻይና ባንዲራ ተተክቶ እላዩ ላይ “ቲዲኤፍ” ከሚል ጽሑፍ ጋር ይታያል። ቲዲኤፍ የትግራይ መከላከያ ኃይሎችን የሚገልጽ ሲሆን እነዚህ ሀይሎች የትግራይ ክልልን ባንዲራ ነው የሚጠቀሙት።
እንዲሁም የወታደሮቹ መኪና የሰሌዳ ቁጥር የሌለው ሲሆን የአንዳንዶቹ ወታደሮች እጆች የተለየ ሆኖ ይታያል። ይህም በሰው ሰራሽ አስተውሎ የተፈጠሩ ምስሎች ዋነኛ መገለጫ ነው።
በሰው ሰራሽ አስተውሎ የተሰሩ ምስሎችን መለየት የሚችለውን ሀይቭ ሞደሬሽንን በመጠቀም የተደረገው ተጨማሪ ማጣራትም ምስሉ በሰው ሰራሽ አስተውሎ የመፈጠር ወይም ሀሰተኛ ይዘት የመያዝ ዕድሉ 99.9 በመቶ መሆኑን አረጋግጧል።

ኢትዮጵያ ኤርትራ እና የትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ህወሃት) “ጦርነት ለመግጠም” ወታደራዊ ጥምረት ፈጥረዋል ብላ እንደከሰሰች ተዘግቧል። ሆኖም ህወሃት ይህንን ክስ ውድቅ አድርጓል።
ከዚህም በላይ ኤርትራ የታጠቁ ቡድኖችን ማለትም የፋኖ ሚሊሻዎችን በኢትዮጵያ የአማራ ክልል ውስጥ እንዳሰለጠነች ሪፖርቶች ያመለክታሉ።
ፔሳቼክ የትግራይ ክልል፣ የኤርትራ እና የኢትዮጵያን ባንዲራዎች ወታደሮች ሲያውለበልቡ ያሳያል በሚል ፌስቡክ ላይ የተለጠፈውን ምስል መርምሮ ሐሰተኛ መሆኑን አረጋግጧል።
ይህ ልጥፍ በፌስቡክ እና በተለያዩ የማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የፔሳ ቼክ የእውነታ መርማሪዎች በተከታታይ የሚያደርጉት የመረጃ ማረጋገጥ እና የተሳሳተ መረጃን የማጋለጥ ተግባር አካል ነው።
እንደ ፔሳቼክ ያሉ ገለልተኛ ሶስተኛ ወገን የእውነት መርማሪ ድርጅቶች ከፌስቡክ እና መሰል የማህበራዊ ድረ ገጾች ጋር በመጣመር የሐሰት ዜናን መለየት እንዲያስችልዎ ይሰራሉ:: ይህን የምናደርገውም በየማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የሚመለከቱት ልጥፍ/ መረጃ መነሻቸውን በማያያዝ እና ጠለቅ ያለ ዕይታ እንዲኖርዎ በማድረግ ነው::
በፌስ ቡክ ላይ የሐሰተኛ መረጃ ወይም የተጭበረበረ የመሰልዎ አጋጣሚ አለ? እንግድያውስ በእዚህ መንገድ ጥቆማ መስጠት ይችላሉ:: እንዲሁም ይህን ተጨማሪ ኢንፎርሜሽን በመጠቀም አጠራጣሪ መልዕክቶችን ለመለየት የፔሳቼክ መንገዶችን ማየት ይችላሉ::

ጽሑፉ በፔሳቼክ ማኔጂንግ ኤዲተር ዶሪን ዋይናኢናህ እንዲታተም ጸድቋል።

ፔሳቼክ የምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የፋይናንስ መረጃ መርማሪ ተቋም ነው:: ካትሪን ጊቼሩ እና ጀስቲን አርንስቴን በተባሉ ሰዎች የተመሰረተ እንዲሁም በአህጉሪቱ ትልቁ የሲቪክ ቴክኖሎጂ እና የጋዜጠኝነት መረጃ ቋት አቅራቢ በኮድ አፍሪካ የተገነባ ነው:: እንደ ጤና : የገጠር ልማት እና የንጹህ ውሃ አቅርቦት በመሳሰሉ መስኮች ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ከመንግስት የሚጠበቁ አቅርቦቶች ላይ የተጨባጩን ዓለም እይታችንን ሊቀርጹ የሚችሉ በይፋ በሚሰራጩ የፋይናንንስ መረጃዎችን ዙርያ ህብረተሰቡ እውነተኛ መረጃን ማገናዘብ እንዲችል ለማገዝ የሚያስችል ድጋፍ ይሰጣል:: ፔሳቼክ ሚድያዎች የሚያቀርቡትን ጥንቅርም ይፈትናል:: የበለጠ መረጃ ለማግኘት pesacheck.org. ይጎብኙ::
ፔሳቼክ ኮድ ፎር አፍሪካ ከዶቼቬለ አካዳሚያ ባገኘው ድጋፍ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሚድያዎች እንዲሁም የሲቪክ ተቋማት ጋር በመተባበር ኢኖቬት አፍሪካ ፈንድ በሚለው መስመሩ የሚያቀርበው እንቅስቃሴ ነው።



